Fana: At a Speed of Life!

በነዳጅ እና የተሽከርካሪ መለዋወጫ ጭማሪ ምክንያት የትራንስፖርት ታሪፍ ማስተካከያ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በነዳጅ እና የተሽከርካሪ መለዋወጫ ጭማሪ ምክንያት የትራንስፖርት ታሪፍ ማስተካከያ መደረጉን የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ከሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የተደረገውን የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ መሰረት በማድረግ÷ የአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ ተሸከርካሪዎች ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ አድርጓል፡፡
የተደረገው የታሪፍ ማስተካከያ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
በደረጃ አንድ በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0 ነጥብ 5360 ሲሆን አዲሱ ታሪፍ 0 ነጥብ 5600 ብር በኪሎሜትር ሆኗል፡፡ ጭማሪ በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 0240 ሳንቲም ነው፡፡
ደረጃ አንድ በጠጠር መንገድ በሰው በኪሎሜትር ነባር ታሪፍ 0 ነጥብ 6150 ሲሆን አዲስ ታሪፍ 0 ነጥብ 6464 ነው፡፡ ጭማሪ በሰው በኪሎሜትር 0 ነጥብ 0314 ሳንቲም ይሆናል፡፡
ደረጃ ሁለት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0 ነጥብ 5120 ሲሆን አዲስ ታሪፍ 0 ነጥብ 5420 ነው፡፡ ጭማሪ 0 ነጥብ 0300 ሳንቲም፡፡
ደረጃ ሁለት በጠጠር መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.5680 ሲሆን አዲስ ታሪፍ 0.6054 ብር ነው፡፡ ጭማሪ በኪሎሜትር 0.0374 ሳንቲም፡፡
ደረጃ ሶስት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0 ነጥብ 4750 ሲሆን አዲስ ታሪፍ 0 ነጥብ 5081 ነው፡፡ ጭማሪ በኪሎሜትር 0 ነጥብ 0331 ሳንቲም ነው፡፡
ደረጃ ሶስት በጠጠር መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0 ነጥብ 5360 ሲሆን አዲስ ታሪፍ 0 ነጥብ 5735 ነው፡፡ ጭማሪ በኪሎሜትር 0 ነጥብ 375 ሳንቲም ነው፡፡
የታሪፍ ስሌቱ በ100 ኪሎ ሜትር ሲታይ፡-
በደረጃ አንድ ተሸከርካሪ በ100 ኪሎሜትር ለአንድ ሰው ነባር ታሪፍ በአስፋልት መንገድ ብር 53 ነጥብ 60 ሲሆን÷ በአዲሱ ታሪፍ ብር 56 ነጥብ 00 ሆኗል፡፡ ጭማሪ በ100 ሊሎሜትር ብር 2 ነጥብ 40 ነው፡፡
በደረጃ ሁለት ተሸከርካሪ በ100 ኪሎሜትር ለአንድ ሰው ነባር ታሪፍ በአስፋልት መንገድ ብር 51 ነጥብ 20 የሚያስከፍል ሲሆን÷ በአዲሱ ታሪፍ ብር 54 ነጥብ 20 ሆኗል፡፡ ጭማሪ በ100 ኪሎሜትር ብር 3 ነጥብ 00 ነው፡፡
በደረጃ ሶስት ተሸከርካሪ በ100 ኪሎሜትር ለአንድ ሰው ነባር ታሪፍ በአስፋልት መንገድ ብር 47 ነጥብ 50 የሚያስከፍል ሲሆን በአዲሱ ታሪፍ ብር 50 ነጥብ 81 ያስከፍላል፡፡ ጭማሪ በ100 ኪሎ ሜትር ብር 3 ነጥብ 31 ነው፡፡
ታሪፉ ከላይ በተገለጸው መሰረት ከዛሬ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መሆን የጀመረ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.