Fana: At a Speed of Life!

“ማንም አገር ከኢትዮጵያ ጋር ተዋግቶ ማሸነፍም ሆነ ማፍረስ አይችልም” አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ማንም አገር ከኢትዮጵያ ጋር ተዋግቶ ማሸነፍም ሆነ ማፍረስ አይችልም” ሲሉ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ወቅታዊና አገራዊ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ እንደገለጹት፥ “ማንም አገር ከኢትዮጵያ ጋር ተዋግቶ ማሸነፍም ሆነ ማፍረስ አይችልም። ይህ ማለት ግን ጠላቶች እጃቸውን አጣጥፈው ይቀመጣሉ ማለት አይደለም” ብለዋል።

ችግሩ ውስብስብ በመሆኑ በትኩረት ማየት እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡

በዲፕሎማሲ፣ በመረጃ ጦርነት እና በተላላኪዎች ከፍተኛ ዘመቻ ተደርጓል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ እስካሁን በዚህ ሂደት ኢትየጵያን ማፍረስ አልተቻለም፥ አይቻልምም ነው ያሉት ፡፡

የመካለከያ እና የደህንነት ተቋማት ባለፉት 15 እና 20 ዓመታት ከነበሩበት በእጅጉ የተሻለ ቁመና ላይ መሆናቸውን ያወሱት ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ ÷ ይህን ያደረግነው የሽብር ኃይሎች ኢትዮጵያን ለማፈረስ ያላቸውን መሻት ስምናውቅ ነው ብለዋል፡፡

ለአብንትም በዛሬው ዕለት አሶሳ ላይ እቅድ እንዳላቸውና በተያዘው ሳምንት አዲስ አበባ ውስጥ ከስድስት ጊዜ በላይ ያሰቡት እቅድ መክሸፉንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የጠቀሱት።

ይሁን እንጂ መከላከያን ለማጠናከር ያደረግነው ጥረት አገራችን ካላት ስፋት አንጻር፥ በሁሉም ቦታ ያሉትን ዜጎች ደህንነት በሚገባ መከላከል አልቻልም ነው ያሉት፡፡

የመንግስት ቀዳሚ ተግባር የህዝብን ሰላም ማስከበር መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው፥ ከሕዝብ ጋር በቅንጅት እና በጋራ አገርን መታደግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

አሸባሪዎችን ከዘር ጋር እና ከሃይማኖት ጋር ማያያዝ አስቸጋሪ መሆኑን አንስተው፥ ሰሞኑን አሸባሪው ሸኔ በወለጋ ተወልደው ያደጉ ንጹሃን ዜጎችን በግፍ የጨፈጨፋቸው ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ ዓላማ የለውም ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለዓለም ያላት አስጸዋጽኦ እና ለማደግ ያላት አቅም፥ እድልም ፈታናም አለው ያሉት ጠቅላይ ሚኒሰትሩ÷ የተለያዩ አካላት የሴሯቸውን ስውር ዓላማዎች ለማሳካት በኢትዮጵያ የሚከሰትን ማንሻውንም አሉታዊ ድርጉት አጋንናው እንደሚያቀርቡና ሊጠቀሙበት እንደሚሹ አብራርተዋል፡፡

እነዚህ አገራት በተለይም በሳይበር ጥቃት፣ የተልዕኮ ውጊያ ማለትም ተላላኪዎች እና ባንዳዎች ያሉበት አገር ሲያገኙ “ጨው እያቀመሱ ትርምስ እንዲፈጥሩ ያደርጓቸዋል” ሲሉም አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያለውን አብሮ የመኖር እሴት ለማፍረስ የተመረጡ አካባቢዎች እንዳሉ ጠቁመው፤ በዚህ መሰረትም ኦሮሞ እና አማራን በተቻላቸው አቅምና አጋጣሚ ማፋጀት ነው፣ አማራን እርስ በርስ ማፋጀት እንዲሁም አሮሞን እርስ በርስ ማጋጨት፣ አፋር እና ሶማሌን እንዲሁም ሲዳማ እና ወላይታን ማፋጀት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በእነዚህ ቀጠናዎች በዲፕሎማሲ፣ በመረጃ ጦርነት እና በተላላኪዎች ከፍተኛ ዘመቻ ተደርጓል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ እስካሁን በዚህ ሂደት ኢትየጵያን ማፍረስ አልተቻለም፥ አይቻልምም ነው ያሉት ፡፡

“ማንም አገር ከኢትዮጵያ ጋር ተዋግቶ ማሸነፍም ሆነ ማፍረስ አይችልም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ይህን ማለት ግን ጠላቶች እጃቸውን አጣጥፈው ይቀመጣሉ ማለት እንዳልሆነና፣ ችግሩ ውስብስብ በመሆኑ በትኩረት ማየት እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

“አደጋ ከመድረሱ በፊት ለመከላከል እየተሰራ ነው”

በየትኛውም አካላት የሚቃጣን ጥቃት ለመመከትም መከላከያን ማጠናከር ያስፈልጋል ያሉት ጠቅለይ ሚኒስትር ዐቢይ÷ የመከላከያ እና የደህንነት ተቋማትን ስናጠናክርም በተቻለ መጠን አራት መስፈርቶች የእነዚህ ተቋማት መርህ እንዲሆኑ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

ማንኛውም ዜጋ መከላከያ ውስጥ ሲገባ ተቋሙን የዘር መጠቀሚያ ማድረግ እና የራሱን እምነት ይዞ መከላከያ እና ደህንነት ውስጥ መግባት እና ማስረጽ እንደለሌበት አብራርተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ማንኛውም ግለሰብ ያለውን የግል የፖለቲካ አመለካካት ተቋማቱ ውስጥ ማንጸባረቅም ሆነ መጠቀም እንዲሁም በጥቅም ተታልሎ የአገርን ጥቅም አሳልፎ መስጠት የለበትም ሲሉም አሳስበዋል።

በዚህ መስፈርት ተቋማቱ ላይ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰው፥ አሁን ያለው መከላከያ በእጅጉ የተሻለ ቁመና ላይ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

የሕግ ማስከበርን በተመለከተም መንግስት የሚፈጸሙ የሽብር ድርጊቶችን ለመከላከል ስትራቴጂ ተነድፎ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፣ ለዚህም የመጀመሪያው መንገድ መከላከል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ አንጻር ተቋማትን በማጠናከር አደጋው ከመድረሱ በፊት ለመከላከል እየተሰራ መሆኑን ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የገለጹት።

በተጨማሪም ሊፈጸሙ የሚችሉ ድርጊቶችን ለመከታተል የክትትል አቅምን ለማሳደግ አስፈላጊው ስራ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ሌላኛው መጠበቅ መሆኑን ጠቁመው፥ “የጥቃት ዋና ዋና ትኩረት የሆኑ ፕሮጀክቶችንና ተቋማትን እንጠብቃለን፤ የማንደርስባቸውን ደግሞ ሕዝብ ተደራጅቶ እንዲጠብቃቸው እናደርጋለን” ብለዋል።

አራተኛው መዘጋጀት መሆኑን ያብራሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ÷ ሰው ሞተ ስንባል ተጯጩኸን የምንረሳ ሳይሆን፥ ተጨማሪ ሞት እንዳይኖር በየቀኑ መዘጋጀት እንደሚያስፈልግና ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅ እየተሰራ መሆኑን ነው ያስረዱት፡፡

ፈተናዎች ይበልጥ እያጠነከሩ፣ በፈተና ውስጥ ይበልጥ ወደ ፊት እየተጓዝን እንገኛልን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡

ድርድርን በሚመለከት ገዢው ፓርቲ ድርድሩን ወስኗል ለሚባለውም የኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ ሁል ጊዜ ለሰላም ቅድሚያ እንደሚሰጥ ገልጸው፥ ለሰላምም ሆነ ለጦርነት የምንወስነውም በብሄራዊ ጥቅማችን እና በአገራዊ አንድነታችን ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

ብልጽግና እንደራደር እና ሰላም እንፍጠር ነው ያለው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የኢትዮጵያን መንግስት የሚመራ ፓርቲ እንደመሆኑ ወስኖ የመምራት ሙሉ ህጋዊ ስልጣን አለው ብለዋል፡፡

ከአሸባሪ ጋር ድርድር አይካሄድም የሚባለውን በተመለከተም፥ በሰላማዊ ውይይት የሚፈታ ነገ ካለ ሁሉንም አማራጭ ማየት ተገቢ እና የሚሻል መሆኑን አንስተዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.