Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ከአሰልጣኝ ካሳየ አራጌ ጋር መለያየቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ከአሰልጣኝ ካሳየ አራጌ ጋር በይፋ መለያየቱን አስታውቋል፡፡

አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ከአሜሪካ  ወደ አገር ቤት በመመለስ ላለፉት ሦስት ዓመት የቀድሞ ክለቡ ኢትዮዽያ ቡና ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ሲያገለግል ቆይቷል።

ይሁን እንጅ አሰልጣኙ እና የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ኮንትራት በዛሬው ዕለት የሚጠናቀቅ ሲሆን÷ ክለቡ በይፋ ከአሰልጣኝ ካሳዬ ጋር መለያየቱን  የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ተናግረዋል።

ክለቡ ዓምና በሊጉ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ቢያጠናቅቅም በዘንድሮው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ42 ነጥቦች 6ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁን ተክትሎ የአሰልጣኙ ቆይታ መገታቱን ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ቡና እግርኳስ ክለብ ከአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ታፈሰ ሰለሞን ጋር በይፋ መለያየቱን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.