Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ በንግድና ትራንዚት የሚስተዋሉ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ በንግድ፣ ትራንዚት እና ሌሎች የትብብር ጉዳዮች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ተስማሙ፡፡
 
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ሃላፊዎችን ያካተተ ልዑክ በትናንትናው ዕለት ሶማሌ ላንድ ሃርጌሳ ገብቷል፡፡
 
የልዑካን ቡድኑ አባላት በሃርጌሳ ቆይታቸው ከሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሳ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ መካከል ባለው የንግድ እና የትራንዚት እንዲሁም ሌሎች የትብብር ጉዳዮች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በጋራ መፍታት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መክረዋል፡፡
 
በዚህም በትብብር መስኮቹ የሚስተዋሉ ችግሮችን በቅንጅት ለመፍታት ስምምነት ላይ መደረሱን አምባሳደር ሬድዋን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
 
ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግም የጋራ ኮሚቴ ለማቋቋም መስማማታቸው ነው የተገለጸው፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.