Fana: At a Speed of Life!

የታለመለት ነዳጅ ድጎማን ተከትሎ ሊፈጠር የሚችልን ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመቀነስ ልዩ ቁጥጥር ማድረግ ይገባል – የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት በነዳጅ ላይ የሚያደርገው ድጎማ ወደ ታለመለት ድጎማ ማዞሩን ተከትሎ ሊፈጠር የሚችልን ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመቀነስ ልዩ ቁጥጥር እና ክትትል መደረግ እንዳለበት የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ተናገሩ።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን መምህርና ተመራማሪ ዶክተር ወገኔ ማርቆሰ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ በነዳጅ ግብይት ዙሪያ ያሉ የሌብነት ሰንሰለቶችን መበጣጠስ እና የንግድ ስርዓቱን ማዘመን እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
መንግስት የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተግባራዊ ሲያደርግ ኢኮኖሚውን ለማዳከም የሚሰሩ አሻጥሮች እንደሚኖሩ በማሰብ ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት ይኖርበታልም ነው ያሉት።
ሌላኛው የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ዶክተር ጌታቸው አየለ በበኩላቸው÷ ለህዝብ አገልግሎት ለሚሰጡ የትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች የታለመለት ነዳጅ ድጎማ መደረጉ ተገቢ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ይሁን እንጂ አገር በሌላት ጥሪት አሟጣ የምትገዛውን ነዳጅ በተገቢው መንገድ መጠቀም እና መቆጠብ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በሃይማኖት ወንድራድ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.