Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መካከል ያለውን መልካም ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መካከል በወደብ መሰረተ ልማትና በባህር ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ያለውን መልካም ግንኙነት ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ እና የጂቡቲ የወደቦች እና የነፃ ቀጠናዎች ባለሥልጣን ሊቀመንበር ሚስተር አቡበከር ዑመር ሐዲ በወደብና በባህር ትራንስፖርት አገልግሎት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

ውይይታቸውም፥ በሁለቱ አገራት መካከል በወደብ መሰረተ ልማትና በባህር ትራንስፖርት ዘርፍ ያለውን መልካም ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አሕመድ ሽዴ የተመራ የልዑካን ቡድን ጂቡቲ መግባቱንና ደማቅ አቀባበል የተደረገለት መሆኑንም ከጅቡቲ ወደቦች እና ነፃ ቀጠናዎች ባለስልጣን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.