Fana: At a Speed of Life!

ጣሊያን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በመላው ሀገሪቱ የጉዞ እገዳ ጣለች

አዲስ አበባ፣መጋቢት 1፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጣሊያን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በመላው ሀገሪቱ ህዝባዊ ስብሰባዎችንና የጉዞ እገዳዎችን መጣሏ ተሰምቷል፡፡

ጣሊያን በርካታ ዜጎቿን የገደለባትን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታትና ለመቆጣጠር  የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ  ትገኛለች፡፡

በዚህም ባለፈው እሁድ በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ 16 ሚሊየን ሰዎች እስከ ሚያዝያ ወር መጀመሪያ ድረስ  ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ውሳኔ አሳልፋ ነበር።

በጣሊያን የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ሲሆን በዚህም 20 የሚሆኑ የሀገሪቱ ክልሎችን ማዳረሱ ነው የተነገረው።

በቫይረሱ ምክንያት ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 463 መድረሱ የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ይህንን ተከትሎም ጣሊያን በመላ ሀገሪቱ የጉዞ  እገዳ ከመጣሏም ባለፈ  ሕዝባዊ ስብሰባዎች እና የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ከልክላለች፡፡

የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ÷ ሰዎች  በቤታቸው እንዲቀመጡ ትዕዛዝ ከማስተላለፋቸው በተጨማሪ ለአስፈላጊ ጉዞ ፈቃድ መጠየቅ  ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም  እርምጃው  የዜጎችን ጤንነት ለመጠበቅና ለወረርሽኙ  ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ለመከላከል ነው  ብለዋል፡፡

ጣሊያን ከቻይና ቀጥሎ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ  የከፋ ጎዳት የደረሰባት ሀገር ናት ተብሏል፡፡

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.