Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሽብሩ ከታንዛንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በሁለትዮሽ የጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በታንዛንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሽብሩ ማሞ ከታንዛንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊብራታ ሙላሙላ እና ከታንዛንያ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ሃማድ ማሱን ጋር በወቅታዊ እና የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም÷ አምባሳደር ሽብሩ ማሞ መንግስት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የተፈጠረውን ግጭት በማስቆም ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የተለያዩ ርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በዚህም ያልተገደበ ሰብዓዊ እርዳታ እንዲዳረስ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችን እንዲሁም ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በማቋቋም ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ለማድረግ የተወሰዱ እርምጃዎችን እና ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የሁለቱ ሀገራት የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን የፖለቲካ ምክክር ማስጀመር መፋጠን እንዳለበት፣ ወደ ታንዛንያ ለሚመጡ ኢትዮጵያውያን የቪዛ አሰጣጥን በተመለከተ እና በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ ሲሞክሩ በታንዛኒያ የፀጥታ ኃይሎች ተይዘው በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎችን መንግስት ወደ አገራቸው ለመመለስ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
የታንዛንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊብራታ ሙላሙላ በበኩላቸው÷ የሁለቱ ሀገራት የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን የፖለቲካ ምክክር በአጭር ጊዜ ውስጥ ማስጀመር ተገቢ እንደሆነ ተናግረዋል።
በሕገ ወጥ መንገድ በኬንያ -ታንዛንያ አድርገው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ ሲሞክሩ በታንዛንያ የፀጥታ ኃይሎች ተይዘው በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎችን የኢትዮጵያ መንግስት ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚያደርገውን ጥረት ማጠናከር እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ወደ ታንዛንያ ለሚመጡ ኢትዮጵያዊያን የቪዛ አሰጣጥን (የሪፈራል ቪዛን) በተመለከተ በትኩረት እየተሰራበት እንደሆነ መናገራቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.