Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም የቀረበውን አዋጅ አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ከሰዓት ባካሄደው 16ኛ መደበኛ ስብሰባው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም የወጣውን ረቂቅ አዋጅ አፅድቋል።

የሕግ፣ ፍትሕ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ እፀገነት መንግስቱ ረቂቅ አዋጁን አስመልክቶ የውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ተሻሽሎ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ተልዕኮውን በብቃት ለመወጣት የሚያስችለው ተጨማሪ ስልጣንና ተግባር እንዲኖረው የሚያደርግ መሆኑ ተብራርቷል።

ከቃላትና ሀረጋት ብያኔ ጀምሮ በርካታ የአዋጁ አንቀፆች መሻሻላቸውና አዳዲስ ሀሳቦች መካተታቸው ተገልጿል።

ምክር ቤቱም የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም የወጣውን ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1276/2014 ዓ.ም በአንድ ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ ማፅደቁን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.