Fana: At a Speed of Life!

የግንባታ ማስጀመሪያ እና የሕንጻ መጠቀሚያ ፈቃድ አገልግሎት በኦን ላይን መስጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የግንባታ ማስጀመሪያ እና የሕንጻ መጠቀሚያ ፈቃድ አገልግሎቶችን በኦን ላይን መስጠት ጀመረ።
ባለስልጣኑ ለተገልጋዮች ፈጣንና ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት ለመስጠት የግንባታ ማስጀመሪያ እና የሕንጻ መጠቀሚያ ፈቃድ አገልግሎቶች የኦን ላይን ስርዓት በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል።
የኦን ላይን ስርዓቱ ባለስልጣኑ ለተገልጋዮች የሚሰጠውን አገልግሎት÷ በማዘመን ቀልጣፋ፣ ወጪ ቆጣቢና ከሙስና የጸዳ አሰራርን መተግበር እንደሚያስችለው ተገልጿል፡፡
ተገልጋዮችም ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት ለማግኘት www.Business.gov.et መጠቀም እንደሚችሉ የባለስልጣኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
ባለስልጣኑ የአገልግሎት አሰጣጡንና የአሰራር ስርዓቱን ለማቀላጠፍ፣ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝና አደረጃጀት ተግባራዊ በማድረግ ሲሆን÷በቀጣይም በሌሎች አገልግሎቶች የኦን ላይን አገልግሎት የመስጠት ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.