Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እጣ የሚያወጣባቸውን ቤቶች የሚያስተዳድረው የቴክኖሎጂ ሲስተም ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እጣ የሚያወጣባቸውን ቤቶች የሚያስተዳድረው የቴክኖሎጂ ሲስተም ታዛቢዎች እና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በተገኙበት ተከፍቷል፡፡

ግልፅነትንና  ተጠያቂነትን ለማስፈን እንደሚያግዝ የታመነበት ይህ የቴክኖሎጂ ሲስተም ለአራት ዙር ሙከራ የተደረገበት ሲሆን፥  አምስተኛውና የመጨረሻው ዙር የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ሙከራው ተካሂዶ  ለዕጣ ማውጣት ፕሮግራሙ ዝግጁ እንዲሆን መደረጉ ተገልጿል፡፡

በዛሬው እለትም  የዘርፉ ባለሙያዎች ፣ ገለልተኛ አካላት እንዲሁም ከተመዝጋቢዎች የተወከሉ ታዛቢዎችና የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት በይፋ ተከፍቶ ለእጣው ዝግጁ ተደርጓል፡፡

መተግበርያው በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የበለፀገና ከሚመለከታቸው የመንግስት እና  በግል  ተቋማት  ጭምር ታይቶ የተረጋገጠ መሆኑን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.