Fana: At a Speed of Life!

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እና የአንድነት ፓርክ ሰራተኞች ደም ለገሱ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እና የአንድነት ፓርክ ሰራተኞች በክረምት በጎ ፈቃድ ስራ ደም ለገሱ።
በደም ልገሳው የጽህፈት ቤቱ ሰራተኞች እና አመራሮች ተሳትፈዋል።
የጽህፈት ቤቱ ሰራተኞች በክረምት በጎ ፈቃድ በደም ልገሳ ፣ በአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት እና በአረንጓዴ አሻራ እንደሚሳተፉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሀላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ተፈሪ ፍቅሬ ገልጸዋል ።
ሃላፊው በክረምት በጎ ፈቃድ በአረንጓዴ አሻራ እያንዳንዱ ሰራተኛ አንድ መቶ ችግኝ ይተክላል ብለዋል።
ጽህፈት ቤቱ ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን 35 የአቅመ ደካሞችን ቤት እንደሚያድስም አስታውቀዋል ።
በዓላዛር ታደለ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.