Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የዶዶላ ኢፋ ቦሩ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤትን መረቁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ ከ350 ሚሊየን ብር ላይ በሆነ ወጪ የተገነባውን የዶዶላ ኢፋ ቦሩ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት መርቀዋል፡፡
በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ እንደተገለጸው÷ ትምህርት ቤቱ ከሀገር ውስጥ ቋንቋዎች በተጨማሪ በቻይንኛ፣ ፈረንሳይኛ እና በዓረብኛ ቋንቋዎች ያስተምራል፡፡
ዘመናዊ የ አይ ሲ ቲ ላቦራቶሪ፣ ኮምፒውተር እና ወርክሾፕ ክፍሎች የተሟሉለት መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም ተማሪዎቹ የሚዝናኑበት መዋኛ ገንዳ ፣ አምፊ ቴአትር ቤት፣ ቴኒስ ኳስ፣ ቅርጫት ኳስ፣ መረብ ኳስ፣ ቼዝ እና ቴኳንዶ የሚሰሩበት ዘመናዊ ጂምናዚዬም ማካተቱን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡
ትምህርት ቤቱ የሚገለገልበት የእንስሳት ማርቢያ እንዳለውም ተገልጿል፡፡
በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ የተገነባው የዶክተር ኃይሌ ፊዳ መታሰቢ ሐውልትም ተመርቋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.