Fana: At a Speed of Life!

የጆርጅ ፍሎይድ ገዳይ ዴሬክ ቾቪን ተጨማሪ የ20 አመት እስራት ተፈረደበት

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የጆርጅ ፍሎይድ ገዳይ ዴሬክ ቾቪን በቀረበበት ክስ ተጨማሪ የ20 አመት እስራት ተፈርዶበታል፡፡

የሚኒያ ግዛት ፖሊስ የሆነው ዴሬክ ቾቪን ጆርጅ ፍሎይድን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደሉን ተከትሎ የ22 አመት እስራት ተፈርዶበታል።

ከግድያ ወንጀሉ በተጨማሪ ዴሬክ ቾቪን ባለፈው ታህሳስ ወር የግለሰቡን ሰብአዊ መብት ጥሷል በሚል በቀረበበት ክስ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎበት ነበር።

ጉዳዩን ሲከታተለው የቆየው ፍርድ ቤትም የቀድሞው የፖሊስ ባልደረባ ላይ ተጨማሪ የ 20 አመት እስራት ተፈርዶበታል።

ቾቪን ውሳኔውን ተከትሎ ወደ ፌዴራል እስር ቤት በመዛወር የእስር ጊዜውን የሚያሳልፍ መሆኑን ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል፡፡

ዴሬክ ቾቪን ጆርጅ ፍሎይድን መሬት ላይ በማስተኛትና አንገቱ ላይ በመንበርከክ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቱ እንዲያልፍ ማድረጉ ይታወሳል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.