Fana: At a Speed of Life!

የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ሲሰጥ የነበረው የ2014 ዓም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል እንደገለፁት÷ በፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ላይ ምንም አይነት ችግር አላጋጠመም፡፡

ተማሪዎችም ፈተናውን በጨዋነት እና በእርጋታ እንደወሰዱ የተናገሩት ዳይሬክተሯ ÷ለክልል እና ከተማ አስተዳደር ቢሮዎች  እንዲሁም ፈተናው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የድርሻቸውን ለተወጡ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

በቀጣይም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተናን በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 27 ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ሲሰጥ መቆየቱን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.