Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ እና የምግብ ዋስትና ዓመትን ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት 2022ን የስርዓተ ምግብ እና የምግብ ዋስትና ዓመት እንዲሆን ይፋ ባደረገው መሰረት ኢትዮጵያም የስርአተ ምግብ እና የምግብ ዋስትና ዓመትን ይፋ አድርጋለች።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር የአፍሪካ የስርአተ ምግብ እና የምግብ ዋስትና አመት÷ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለምግብ እና ስርዓተ ምግብ ያለውን ቁርጠኝነት ለማጎልበት እና በአፍሪካ ሀገራት መካከል የእውቀት ልውውጥ ለማካሄድ ያለመ ነው ብለዋል፡፡
የህብረቱ አባላት እና ሌሎች ሀገራትም ተመሳሳይ ተግባር እንዲያከናውኑ በማበረታታት በጋራ በመሆን ለአፍሪካ አወንታዊ የሆነ የስርዓተ ምግብ እድገትን መፍጠር ይቻላል ማለታቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ በበኩላቸው÷ የአፍሪካ ህብረት የምግብና የምግብ ዋስትና ዓመት እንዲሆን ወስኖ ይፋ መደረጉ “በአፍሪካ አህጉር የተመጣጠነ አመጋገብ እና የምግብ ዋስትና አቅምን፣ የግብርና ውጤት የሆኑ ምግብ ስርአቶችን፣ ጤና እና ማህበራዊ ጥበቃ ስርአቶችን ለማጠናከር ያግዛል ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የአፍሪካ ህብረት አመራሮች፣ ሚኒስትሮች እና ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የአጋር ድርጅቶች ኃላፊዎች እና ለጋሾች፣ በፌደራል ደረጃ የምግብ እና ስርዓተ ምግብ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት እና የአለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ተገኝዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.