Fana: At a Speed of Life!

ሠራዊቱ በሕዳሴ ግድብ ቀጣና አስተማማኝ ሰላም በማስፈን ግዳጁን እየተወጣ ይገኛል – ኮሎኔል ንጋቱ አሰፋ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሠራዊቱ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቀጣና አስተማማኝ ሰላም በማስፈን ሌት ከቀን ግዳጁን እየፈፀመ ይገኛል ሲሉ በምዕራብ ዕዝ የሜካናይዝድ ሞተራይዝድ ብርጌድ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ንጋቱ አሰፋ ገለፁ።

የኢትዮጵያ ህዝብ አሻራ ያረፈበት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያለአንዳች የፀጥታ ችግር ግንባታው እየተከናወነመሆኑን ያነሱት ዋና አዛዡ ፥ ሠራዊቱ በቀጣናው አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን ግዳጁን ቀን ከሌት በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

አያይዘውም ብርጌዱ በሕዳሴው ግድብ ሊቃጣ የሚችል ማንኛውንም ዓይነት ጥቃት ለመቀልበስ በሚያስችል ቁመና ላይ መሆኑን መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የክፍለ ጦሩ መቺ ኃይል የሆነው ብርጌዱ በተሰለፈባቸው አውደ ውጊዎች አንፀባራቂ ገድል በመፈፀም ሕዝብ እና መንግስትን ያኮራ ተግባር መፈፀም መቻሉን አስታውሰው ፥ በቀጣይም ጥንካሬውን ይዞ የሚቀጥልበትን አቅም ፈጥሯል ብለዋል።

የብርጌዱ ምክትል አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ሽፈራው ታያቸው በበኩላቸው ፥ ጠላት ቀጣናውን ለማተራመስ በቅጥረኛ ተላላኪ ኃይሎች አማካኝነት በተደጋጋሚ ትንኮሳ ቢሞክርም የሞተራይዝድ ብርጌዱ ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ ሰላም ማስፈን መቻሉን ገልፀዋል።

በቀጣናው የተሰማራው የሜካናይዝድ ብርጌድ በቀጣናው ሊፈጠር ለሚችል የፀጥታ ስጋትን በአስተማማኝ ለመመከት በተጠንቀቅ ሆኖ ግዳጁን በመፈፀም ላይ እንደሚገኝም አዛዦቹ አረጋግጠዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.