Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ከቻይና እና ሕንድ ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት በአዳዲስ የንግድ መስመሮች እያጠናከረች መሆኑ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በጭነት መርከቦች ለቻይና እና ሕንድ የተለያዩ የወጪ ንግድ ሸቀጦች እያቀረበች መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሩሲያ ከዚህ ውሳኔ የደረሰችው ምዕራባውያኑ የጣሉባትን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ተከትሎ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ኢንቴኮ የተሰኘው የሩሲያ የዕቃ ማጓጓዣ መርከቦች አገልግሎት ድርጅት እና የቻይናው ስዊፍት የትራንስፖርት አስተላላፊ÷ የባሕር ላይ የሸቀጦች የንግድ አገልግሎቱን በጋራ እየሰጡ መሆኑን ዘገባዎች ጠቁመዋል።

ሁለቱ ድርጅቶች አገልግሎቱን የሚሰጡት መነሻውን ከሩሲያ ሩቅ ምሥራቅ አካባቢ ከሚገኘው ቮስቶቺኒ ወደ ቻይና የወደብ ከተሞች ነው ተብሏል፡፡

ሀገራቱ በዚህ ዓመት ከሩሲያ ጋር ያደረጉት የንግድ ልውውጥ በከፍተኛ ደረጃ የጨመረ ሲሆን፥ ሩሲያ በአጸፋው የምትሸጥላቸው የኃይል አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ቅናሽ ማድረጓ ተጠቁሟል፡፡

የቻይና ጉምሩክ አገልግሎት መረጃ እንደሚያሳየው ÷ እስከ ፈረንጆቹ ግንቦት ወር መጨረሻ ባሉት ሦስት ወራት ከሩሲያ የ19 ቢሊየን ዶላር የነዳጅ ዘይት፣ ጋዝ እና የድንጋይ ከሰል ግዢ ፈጽማለች፡፡

ሕንድ በበኩሏ በተመሳሳይ ጊዜ ከሩሲያ የ5 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ግዢ መፈጸሟ ተገልጿል፡፡

ሀገራቱ ቀስ በቀስ ከሩሲያ የሚፈጽሙት ግብይት በብዙ ዕጥፍ ሊያድግ እንደሚችል መነገሩን አር ቲ ዘግቧል፡፡

ቻይና እና ሕንድ ምዕራባውያኑ በሩሲያ ላይ የጣሉትን ማዕቀብ መቃወማቸው እና ከሩሲያ ጋር መደበኛ የኢኮኖሚ እና የንግድ ትብብር እንደሚቀጥሉ ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.