Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጃፓኑ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ አሳዛኝ አሟሟት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጃፓኑ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ አሳዛኝ አሟሟት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለጸ፡፡

ሚኒስቴሩ አክሎም ፥ ለህልፈተ ህይወታቸው ምክንያት የሆነውን አሳዛኝ ድርጊት በጽኑ አውግዟል ።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በኢትዮጵያና ጃፓን መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውንም ነው የገለጸው ።

የአፍሪካ ጃፓን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ እንዲጠናከር በማድረግ የቶኪዮ ዓለም አቀፍ የአፍሪካ ልማት መድረክ (ቲካድ)ን በማጠናከርም የጎላ ሚና የተጫወቱ መሪ እንደነበሩ ሚኒስቴሩ አንስቷል።

በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር በደረሰው አሰቃቂ ሞት የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለወዳጅ የጃፓን ህዝቦች፣ ለጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን መመኘቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.