Fana: At a Speed of Life!

የአንጎላ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆሴ ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶስ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አንጎላን ለአራት አስርት አመታት የመሩት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጆሴ ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶስ በ79 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በስፔን ባርሴሎና የህክምና ክትትል ላይ እያሉ መሞታቸውን የአንጎላ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል፡፡

በአፍሪካ ለረጅም ጊዜ በስልጣን ላይ ካሉ መሪዎች አንዱ የሆኑት ጆሴ ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶስ ከአምስት አመት በፊት ስልጣን በመልቀቅ በ 2017 በፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንኮ ተተክተዋል፡፡

ምንጭ ፡ ሲጅቲኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.