Fana: At a Speed of Life!

የጫት የወጪ ምርት ሽያጭ ውል አፈጻጸም ላልተወሰነ ጊዜ ተቋረጠ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጫት የወጪ ምርት ሽያጭ ውል አፈጻጸም ላልተወሰነ ጊዜ መቋረጡን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ÷ኢትዮጵያ ለውጪ ገበያ ከምታቀርባቸው ዋና ዋና የግብርና ምርቶች አንዱ የጫት ምርት መሆኑን አንስቷል፡

ይሁን እንጂ ከዘርፉ የሚገኘው የውጪ ምንዛሬ ገቢ ግኝት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ቢሆንም፥ በጫት ምርት የላኪነት የንግድ ስራ ፈቃድ አተገባብር፣ በጫት ምርት ውል አግባብና አፈፃፀም፣ በመላኪያ ፈቃድ አሰጣጥ እና በጫት ምርት የውጪ ምንዛሬ ክፍያ አፈጻጸም ችግሮች የሚታዩበት በመሆኑ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ገቢ እያጣች መሆኑን አመላክቷል፡፡

የጫት ምርት የወጪ ንግድ ፍትሃዊ እና አኩል ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የጫት ምርት በውል ምዝገባ እና አስተዳደር አሰራር ስርዓት ውስጥ በማካተት የጫት ምርት የውል ምርት ምዝገባና አፈፃፀም አተገባብርን በቁጥር 01.130/32138 ግንቦት 22 ቀን 2022 በተፃፈ ደብዳቤ ማሳወቁን ሚኒስቴሩ አስታውሷል፡፡

ስለሆነም በውል ምዝገባ አፈፀም ስርዓት ላይ ያሉ ችግሮችን በማስተካል በቋሚነት የአሰራር ስርዓት መዘርጋት እስከሚቻል ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ የጫት የውል ምርት ምዝገባ መቋረጡን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.