Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ፖሊስ ለዒድ አል አድሃ በዓል ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2014 (አፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ በነገው ዕለት ለሚከበረው 1 ሺህ 443ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ይፋ አደረገ፡፡

1 ሺህ 443ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አፈስላጊውን ዝግጀት አጠናቆ ወደ ሥራ መግባቱን አስታውቋል፡፡

የኢድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቀ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑም ነው የገለጹት፡፡

ለበዓሉ አከባበር ሀገራችን ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ልዩ ዝግጅት ከመደረጉም ባሻገር ከእምነቱ አባቶችና ከፈቃደኛ ወጣቶች ጋር በበዓሉ አከባበር ዙሪያ አስቀድሞ ተገቢውን ውይይት በማድረግ ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል፡፡

የበዓሉ ታዳሚዎች በየአካባቢያቸው በዓሉን ሲያከብሩም ሆነ ወደ ሶላቱ ሲመጡ እንደወትሮው ሁሉ የፀጥታ ኃይሉን መስተንግዶና ትዕዛዝ በማክበር ተባባሪ እንዲሆኑ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ህብረተሰቡ ለፀጥታው ስራ ስኬታማነት እያደረገ ላለው ቀና ትብብር ግብረሃይሉ ምስጋናውን እያቀረበ ትብብሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

ከፀጥታ ጋር ተያያዥ መረጃ ወይም ጥቆማ ለመስጠት በ991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና 01- 11 -11- 01 -11፣ 01- 11- 26- 43- 59፣ 01- 11- 01- 02- 97፣ መጠቀም እንሚቻል ገልጿል።

በዓሉን አስመልክቶ የሚካሄደው የሶላት ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ፡-

ከቦሌ አየር መንገድ ፣ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ወይም ኦሎምፒያ አደባባይ አካባቢ

ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ ለገሃር እንዲሁም ከቦሌ መድሃኔአለም ፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ

ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻ ወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት

ከፒያሣ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቸርችል ጎዳና ቴዎድሮስ አደባባይ

ከተክለ ኃይማኖት ፣ በሚቲዮሮሎጂ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሚቲዮሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ

ከተክለ ኃይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር አካባቢ

ከሲኒማ ራስ በጎላ ሚካኤል ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ

ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቴአትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ

ከባሻ ወልዴ ችሎት ፣ በኦርማ ጋራዥ ወደ ፍል ውሃ መስኪድ የሚወስደው መንገድ ንግድ ማተሚያ ቤት

ከጎፋ ፣ በቂርቆስ ቤተ-ክርስቲያን ወደ ለገሃር አዲሱ መንገድ የሚወስደው መንገድ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን መስቀለኛው ላይ

ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ

ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር
ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከለሊቱ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ መንገዶቹ ዝግ ይሆናሉ፡፡

ከሳሪስ በጎተራ ወደ ለገሃር የሚመጡ ከባድ ተሽከርካሪዎች ከአጎና ሲኒማ ማለፍ እንደማይችሉ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡

በመሆኑም አሽከርካሪዎች ከፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠውን መረጃ ተገንዝበው የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶች እንዲጠቀሙ እና ለፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በመጨረሻም ለእምነቱ ተከታዮች በዓሉ የፍቅር ፣ የሰላምና የደስታ እንዲሆን የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ መልካም ምኞቱን ገልጿል ፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.