Fana: At a Speed of Life!

የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ከንቲባዎች ለኢድ አል አድሃ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ከንቲባዎች ለ1 ሺህ 443ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው ባስተላለፉት መልዕክት የኢድ አል አድሀ (አረፋ ) በዓል ህዝበ ሙስሊሙ በድምቀት ከሚያከብራቸው በዓላት መካከል አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።

በዓሉ በምዕመናን ዘንድ ትልቅ ትርጉም ያለው ሲሆን የአንድነት እና የአብሮነት እሴቶቻችን በጉልህ የሚንጸባረቁበት በዓል ነው ብለዋል።

የተራበን ማብላት፣ የተቸገረን መርዳት እንዲሁም የታረዘን ማልበስ የአረፋ በዓል ልዩ መገለጫ መሆኑን ጠቅሰው፥ ሙስሊሙ ማህበረሰብም እንደ ከዚህ ቀደሙ የጋራ አንድነቱን በማጠናከር እምነቱ በሚያዘው መሰረት አቅመ ደካሞችን በመርዳት ያለውን በማካፈል በዓሉን እንዲያከብር ጥሪ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል በዓሉን በማይመች ሁኔታ ላይ ለሚያሳልፉ ወገኖች ማዕድ በማጋራት አለኝታነትን ማሳየት ይገባልም ነው ያሉት።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፥ “በዓሉን ስናከብር መልካም እሴቶቻችንን በማጠናከር እና የተቸገሩ ወገኖቻችንን በመርዳት መሆን ይገባል ብለዋል።

በተጨማሪም የ”ሰላማችን ዋልታ የሆነውን አብሮነታችንን እና ወንድማማችነታችንን በማጠናከር እንዲሆን እመኛለሁ” ነው ያሉት በመልዕክታቸው።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.