Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግሮች ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና የትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግሮችና የመፍትሄ አማራጮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ በከተማዋ ያሉ የትራንስፖርት ችግሮችን ለመፍታት ከከተማ አስተዳደሩ እንዲሁም ከሚኒስቴር መስርያ ቤቱ ተወካዮች በተገኙበት የተለያዩ የአጭርና የረጅም ጊዜ የመፍትሄ አማራጮች ላይ መክረዋል፡፡
በዚህም መሰረት በተለይ አሁን ያለውን የትራንስፖርት እጥረት ለመቅረፍ በጊዜያዊነት የፐብሊክ አውቶብሶች ወደ ትራንስፖርት ስምሪት የሚገቡበትን የመፍትሄ አማራጭ ለመጠቀም ስምምት ላይ ተደርሷል፡፡
የድጋፍ ሰጪ አውቶብሶችም የመፍትሄው አካል እንደሚሆኑ መገለጹን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
በቀጣይ የሚተገበሩ መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጡ ዘመናዊ የከተማ ትራንስፖርት አማራጮች ላይም በሰፊው ተመክሮባቸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.