Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ 1443ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል የሶላት ስነ-ስርዓት በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በመዲናዋ 1443ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል የሶላት ስነ-ስርዓት በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
1443ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በላም እንዲከበር የፀጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ወቅታዊውን የፀጥታ ሁኔታ ያገናዘበ ዕቅድ በማውጣት ዝግጅት አድርጎ ወደ ስራ መግባቱ የሚታወቅ ነው፡፡
ኀብረተሰቡንና የዕምነቱ ተከታይ በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር በተሰራው ሥራ በአዲስ አበባ ስታዲዮም ዙሪያ የተከናወነው የሶላት ስነ- ስርዓት በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ሥነ-ሥርዓቱ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የበዓሉ ታዳሚዎች ላሳዩት ቀና ተባባሪነት እና ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ተግባራቸውን በብቃት ለተወጡ የፀጥታ አካላት የአዲስ አበባ ፖሊስ በፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ስም ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
ቀሪው የበዓል አከባበር ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥል በየአካባቢው በቂ የፀጥታ ኃይል ተመድቦ ተግባሩን እየተወጣ መሆኑንን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ህብረተሰቡ ከፀጥታ ጉዳይ ጋር ተያያዥ መረጃ ወይም ጥቆማ ለመስጠት በ991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮች እና 01- 11 -11- 01 -11፣ 01- 11- 26- 43- 59፣ 01- 11- 01- 02- 97 መጠቀም ይችላል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.