Fana: At a Speed of Life!

የአረፋ በዓል ሲከበር በመተጋገዝና በመደጋገፍ መሆን እንዳለበት የሃይማኖት አባቶች ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአረፋ በዓል ሲከበር በመተጋገዝና በመደጋገፍ እንዲሁም የፈጣሪን ትዕዛዝ በመፈጸም መሆን እንደሚገባ የእስልምና ሃይማኖት አባቶች ገለጹ፡፡
1443ኛው የኢድ ሶላት (ዐረፋ) በዓል በሐረር ከተማ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ የሐረር ከተማ እና አካባቢው ሕዝበ ሙስሊሞች በተገኙበት በጀምዐ መስጅድ ተከናውኗል፡፡
የሶላት ስነ ስርአቱን የመሩት የሀረር ጀምዐ መስጅድ ኢማም ሼክ ሙክታር ሙባሪክ÷ የአረፋ በዓል ሲከበር የተቸገሩትን በመረዳትና በአብሮነት ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የአረፋ በዓል ሲከበር በመተጋገዝና በመደጋገፍ እንዲሁም የፈጣሪን ትዕዛዝ በመፈጸም መሆን እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡
ሕዝበ ሙስሊሙ ለሰላምና ለሀገር አንድነት የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
ሶላቱ ከተከናወነ በኋላ ሌሎች ሃይማኖታዊ ስርዓቶችም ተካሂደዋል።
በተሾመ ኃይሉ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.