Fana: At a Speed of Life!

አካባቢያችን የአሸባሪዎች መደበቂያ እንዳይሆን ከመከላከያ ሰራዊት ጎን እንቆማለን – የሀሮሰቦ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አካባቢያችን ሸኔን ጨምሮ የሌሎች አሸባሪዎች መደበቂያ እንዳይሆን ከሰራዊቱ ጎን እንቆማለን ሲሉ በቄለም ወለጋ ዞን የሀሮሰቦ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን በዳሌሰዲ ወረዳ የሀሮሰቦ ከተማ ነዋሪዎች በአካባቢው ሰላምና ፀጥታ ዙሪያ ከመከላከያ ሰራዊት አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በስፍራው ግዳጅ እየፈፀመ ያለው ክፍለ ጦር አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል ተክሉ ሁሪሣ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት፥ የአካባቢያችሁን ሰላምና ፀጥታ የሚያውኩ አሸባሪ ኃይሎች በንቃት ለመጠበቅ ከመከላከያ ሠራዊታችን ጋር በቅንጅት መስራት አለባችሁ ብለዋል።

የውጭ ጠላቶቻችን ተላላኪ ሆነው ሀገር ለማፍረስ የተሰለፉ እንደ ሸኔ ያሉ አሸባሪዎችን ለመደምሰስ የሁላችንም ተሳትፎ ያስፈልጋል ማለታቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

የዚህ ዓላማ ቢስ አሸባሪ ኃይል ተሳታፊዎችን ለይቶ ለሕግ ማቅረብ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑንም አስገንዝበዋ፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፥ የተጀመረውን ህግ የማስከበር ዘመቻ በመደገፍ ከመንግስት ጎን በመሆን ወረዳው የሸኔም ሆነ የሌላ አሸባሪ አካል መደበቂያ እንዳይሆን ከሰራዊቱ ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.