Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የፎረንሲክ ዲ ኤን ኤ ምርመራ ላቦራቶሪ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የፎረንሲክ ዲ ኤን ኤ (የዘረመል) ምርመራ ላቦራቶሪ ተመረቀ።

ከ1 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ወጪ የተደረገበት ላቦራቶሪው በኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታል ውስጥ የተቋቋመ ሲሆን፥ ወደ ስራ መግባት የሚያስችለው ደረጃ ላይ መድረሱን ተከትሎ ዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና አዛዥ ኮሚሽነር ጀኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ላቦራቶሪው የኢትዮጵያ ፖሊስን የምርመራ አቅም የተሻለ ደረጃ ለማድረስ ይረዳል ብለዋል።

ለምርመራ ስራው ብቁ ባለሙያዎች መሟላታቸውን ጠቁመው፥ በፍትህ ስርዓቱ ላይ ተጨባጭ እና አስተማማኝ መረጃን ለማቅረብ እንደሚረዳም ተናግረዋል፡፡

ቀደም ሲል የተለያዩ የወንጀልና ወንጀል ነክ ጉዳዮች የሚመረመሩት በዐሻራ ብቻ ነበር ፥ ተጨማሪ የዲ ኤን ኤ ሞርመራዎችን ግን ወደዉጭ በመላክ የምርመራ ስራ ይከናወን ነበር ፣ ለዚህም የራሱን የዉጭ ምንዛሬ ይጠይቅ እንደነበር ኮሚሽነር ጀነራሉ ተናግረዋል ፡፡

በሀገር ዉስጥ አገልገሎት እንዲሰጥ የታሰበዉ የዘረመል ላብራቶሪዉ ከፍተኛ ወጪንና የዉጭ ምንዛሬ ያስቀራል ብለዋል ።

የዲ ኤን ኤ (የዘረመል ላቦራቶሪው) በሰው ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ነገሮችን በመርመር አቅሙ ወንጀል በተፈፀመበት ቦታ የሚገኝን የተለያየ ፈሳሽና መሰል ነገሮች በመመርመር ማወቅ ያስችላል፡፡

ላቦራቶሪው በውስጡ የአጥንትና ሌሎችም ከዘረመል ጋር የተያያዘ መመርመሪያ መሳሪያዎች ተሟልተውለታል፡፡

ላቦራቶሪው የመረጃ ቋት በመፍጠርም ከአለም አቀፍ ፖሊሶች መረጃዎችን በመቀያየር ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን የመከላከል አቅምንም ማሳደግ ያስችላል ነው የተባለው፡፡

ቀደም ሲል ወደ ውጭ በመላክ የሚደረገው የዲ ኤን ኤ ምርመራ በትንሹ ከ50 ሺህ ብር ጀምሮ ለምርመራ ወጪ እንደሚጠቅበትና በሀገር ውስጥ የተቋቋመው የዲ ኤን ኤ ምርመራ ላቦራቶሪ ግን ከዚህ በቀነሰ ወጪ አገልግሎትን እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

ከፍርድ ቤት እና ከፖሊስ ለሚቀርቡ ጥያቄዎችም ቅድሚያ ተሰጥቶ እንደሚሠራም ተመላክቷል፡፡

ፀጋዬ ወንድወሰን

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.