Fana: At a Speed of Life!

የጉራጌ ዞን የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓልን በመቄዶንያ የአረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል አከበረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉራጌ ዞን አስተዳደር 1443ኛውን የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል በአዲስ አበባ መቄዶንያ የአረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሯል፡፡
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ መሀመድ ጀማል ባደረጉት ንግግር÷ የአረፋ በዓልን የትንሿ ኢትዮጵያ መገለጫ በሆነውና የሀገር ባለውለታዎች፣ የነገ ተስፋ ከሚሆኑ ወጣቶች ጋር በመቄዶንያ ማዕድ በማጋራት በማክበራችን ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል።
ለተቋሙ ግንባታ የሚውል 500 ሺህ ብርና የተለያዩ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ የአልባሳት እና ሌሎች ድጋፎችን አድርገዋል፡፡
ዞኑ ከመቄዶንያ የአረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ጋር በመተባበር ከ100 በላይ ደጋፊ የሌላቸው ወገኖች ወደ ማዕከሉ በማስገባት እንዲደገፉ ማድረጉ ተገልጿል፡፡
በወልቂጤ ከተማ የአንድ ሄክታር የግንባታ ቦታ ለማዕከሉ ማስረከባቸው የተናገሩት አቶ መሀመድ÷ ግንባታው እስከሚጠናቀቅም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሂሩት ካሳው እንደገለጹት÷ የጉራጌ ሕዝብ አካባቢ ድንበር የማይወስነው በመሆኑ የአረፋ በዓልም በመቄዶንያ የአረጋውያንና አዕምሮ ማዕከል በመገኘት ከአቅመ ደካሞች ጋር ማክበራቸው ትልቅ መልዕክት አለው ማለታቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.