Fana: At a Speed of Life!

ኤሎን መስክ ትዊተርን ለመግዛት ከገባው የ44 ቢሊየን ዶላር ስምምነት እራሱን አገለለ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለማችን ቁጥር አንዱ ቢሊየነር ኤሎን መስክ ትዊተርን ለመግዛት ያቀረበውን የ44 ቢሊየን ዶላር የግዢ ስምምነት ራሱን አገለለ።
ኤሎን መስክ በሚያዝያ ወር ትዊተርን ለመግዛት ከወሰነ በኋላ በርካታ የግዢ ስምምነቶች አለተከበሩም በማለት ነው ከስምምነቱ ራሱን ያገለለው።
መስክ ውሳኔውን ለመሰረዝ ትዊተር ስለ አላስፈላጊ መልእክት እና ሀሰተኛ አካውንቶችን በተመለከ በቂ መረጃ አለመሰጠቱን በምክንያትነት አንስቷል።
ይሁን እንጂ ትዊተር ስምምነቱን ለማስፈጸም ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዕቅድ እንዳለው ተናግሯል።
“የትዊተር ቦርድ ከመስክ ጋር በተደረሰው ዋጋ እና ደንቦች መሠረት ስምምነቱ ተፈጻሚ እንዲሆን ጽኑ ፍላጎት አለው” ሲሉ የትዊተር ቦርድ ሰብሳቢ ብሬት ቴይለር በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።
ይህ አገላለፃቸውም በሁለቱ ወገኖች መካከል ጥብቅና እና ረጅም ጊዜ ሊወስድ የሚችል የህግ ጦርነት ሊመሰረት እንደሚችል አሳይቷል፡፡
የመጀመሪያው የውህደት ስምምነትም 1 ቢሊዮን ዶላር የመለያያ ክፍያን ያካትታል መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.