የጋምቤላ ክልል የ2014 የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል የ2014 በጀት ዓመት የሴክተር መሥሪያ ቤቶች የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
የአፈፃፀም ሪፖርት ግምገማው ለሁለት ቀናት በሚኖረው ቆይታ÷ በ2014 በጀት ዓመት በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች የተከናወኑ ሥራዎች ሪፖርት ቀርበው ውይይት እንደሚካሄድበት ይጠበቃል።
በሪፖርት ግምገማው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ የክልሉ አመራሮችና ባለሙያዎች መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ መላክታል፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!