Fana: At a Speed of Life!

1443ኛው ዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ1443ኛው ዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በመላው ኢትዮጵያ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሕዝቡን ከጎኑ በማሰለፍና ከሌሎች የፀጥታና ደህንነት ተቋማት ጋር በመቀናጀት÷ በዓሉ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የሕዝቡን ፀጥታና ደህንነት የማስከበር ስራውን በብቃት መወጣቱን ገልጿል፡፡
በጥበቃው ላይ የተሰማሩት የፖሊስ ሰራዊት አባላት ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ከራሳቸው በፊት ሕዝቡን በማስቀደም የተሰጣቸውን ሀገራዊ ተልዕኮ በብቃት በመወጣት የታለመውን ግብ ማሳካታቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፖሊስ የተሰጠውን መግለጫ ከግምት ውስጥ በማስገባት በዓሉ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ መላው ሕዝብ እንዲሁም የፀጥታና ደህንነት አካላት ላደረጉት ቀና ትብብርና ድጋፍ ፖሊስ ምስጋና አመስግኗል፡፡
በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸው ድርሻ ለተወጡ የእስልምና ሃይማኖት አባቶች እና ተከታዮች፣ በዓሉን ላስተባበሩ ወጣቶች የኢትየጵያ ፌዴራል ፖሊስ ምስጋና አቅርቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.