Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ለደቡብ ሱዳን የነፃነት ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የደቡብ ሱዳን 11ኛ ዓመት የነፃነት ቀንን አስመልክተው ለሀገሪቱ መንግሥት እና ሕዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ለድቡብ ሱዳን አቻቸው ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ባስተላለፉት መልዕክት÷ በኢትዮዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት እንዲሁም በራሳቸው ስም ለደቡብ ሱዳን ሕዝብ እና መንግሥት እንኳን ለ11ኛ ዓመት የነፃነት ቀን በዓላችሁ አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

የሁለቱ እህትማማች ሀገራት ግንኙነትም የጋራ ተጠቃሚነት መርህን መሰረት በማድረግ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን በደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.