Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እና ቻይና የፍራፍሬ ግብይትነን ማሳለጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ደዋኖ ከድር ከቻይና ፍራፍሬ ግብይት ማህበር ምክትል ሊቀመንበር ጃን ችንፈንግ ጋር የሁለቱን አገራት የፍራፍሬ ግብይት ማሳለጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡

አምባሳደር ደዋኖ የኢትዮጵያ መንግሥት የፍራፍሬ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ለአብነትም የአቮካዶ ምርት በስፋት እየተመረተና ወደ ውጭ ገበያ እየተላከ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

አምባሳደር ደዋኖ የቻይና ፍራፍሬ ግብይት ማህበር የኢትዮጵያን የፍራፍሬ ምርቶች ለቻይናውያን ተጠቃሚዎች ለማስተዋወቅ የበኩሉን እገዛ እንዲያደርግም ጠይቀዋል፡፡

ጃን ችንፈንግ በበኩላቸው÷ ቻይና ከፍተኛ የፍራፍሬ አምራች አገር መሆኗን አውስተው÷ የተጠቃሚው ቁጥርም ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ማህበሩ ከኤምባሲው ጋር ተቀራርቦ በመስራትና የሁለቱን አገራት የንግድ ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ ፍላጎት ያለው መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡

በዘርፉ ከሚሰሩ የኢትዮጵያ ኩባንያዎች ጋር በመተባበር የጋራ ተጠቃሚነትን ማጎልበት እንደሚቻል መግለጻቸውንም በቻይና ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.