Fana: At a Speed of Life!

የዐረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ የማጋራት መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች እና በመተከል ዞን የዳንጉር ወረዳ ወጣቶች የዐረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ ድጋፍ ለሚሹ የሕብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋርተዋል፡፡
 
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂር ሀብታሙ ኢተፋ፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በወረዳ 04 ለሚኖሩና ድጋፍ ለሚሹ የሕብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ የማጋራት መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡
 
ሚኒስትሩ ማዕድ የማጋራት መርሐ ግብር ኢትዮጵያውን ባለን በዓላትን አብሮ የማሳለፍ ልማድ መሠረት የዒድ አል አደሐ አረፋን በዓል አብሮ ለማሻለፍ እና በተቋሙና በአካባቢው ማኅበረሰብ መካከል ያለውን ግንኙነትና ቤተሰባዊነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
በተመሳሳይ በመተከል ዞን በዳንጉር ወረዳ የማንቡክ ከተማ ተወላጆች በጎ አድራጎት ማህበርና እና የመግንስት ተቋማት በዓሉን ምክንያት በማድረግ በሰላም ማስከበር ዘመቻው ለተሰው ቤተሰቦች ለበዓሉ የሚሆኑ ስጦታዎችን አበርክተዋል።
 
ወጣቶቹ ”ማህበራዊ ሚዲያን” ለመልካም ተግባር ለማዋል በሚል መርሐ ግብር ገቢ በማሰባሰብ በህግ ማስከበር ዘመቻው ለተሰው ቤተሰቦች ድጋፍ ማድረጋቸውን ከመተከል ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
የዳንጉር ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሃብታሙ ባማኑየቀጠናውን ሰላም ለማስፈን መስዋዕትነት የከፈሉ የሚሊሻ አባላት ለሀገር ለከፈሉት የህይወት ዋጋ ትውልድ በጀግንነት ሲያስታውሳቸው እንደሚኖር ገልጸው÷ የቤተሰብ አባላትን ለመደገፍ የሚደረገው ርብርብ ቀጣይነት እንዳለው ገልጸዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.