Fana: At a Speed of Life!

በበጀት ዓመቱ 20 ሺህ 558 ኑሯቸውን በጎዳና ያደረጉ ዜጎችን በማንሳት ወደ መደበኛ ሕይወት የመመለሥ ሥራ ተሰርቷል-ዶ/ር ኤርጎጌ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ 20 ሺህ 558 ኑሯቸውን በጎዳና ያደረጉ ዜጎችን ከጎዳና በማንሳት ወደ መደበኛ ሕይወት የመመለሥ ሥራ መሠራቱን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተሥፋዬ ገለጹ፡፡

ዶክተር ኤርጎጌ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ÷ በ2014 በጀት ዓመት 6 ሺህ 267 ሕጻናት፣ 6 ሺህ 83 እናቶች ከልጆቻቸው ጋር፣ 4 ሺህ 107 አረጋውያን፣ 4 ሺህ 107 ወጣቶች እና ጎልማሶች በአጠቃላይ 20 ሺህ 558 ኑሯቸውን በጎዳና ያደረጉ ዜጎችን ከጎዳና በማንሳት ወደ መደበኛ ሕይወት እንዲመለሱ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም ችግሩ ከምንጩ እንዲፈታ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት እና ከመላው ማኅበረሰብ ጋር ሠፊ ሥራ እየሠራን እንገኛለን ነው ያሉት ሚኒስትሯ።

ዶክተር ኤርጎጌ ÷ ሕይወታቸውን በጎዳና ያደረጉ ዜጎችን በማንሳት እና ወደ መደበኛ ሕይወት በመመለሥ ሂደት ድጋፍ ላደረጉት ዓለም ባንክና ሀገር በቀል የተራድዖ ድርጅቶችናተቋማት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በዛሬው ዕለትም “ብራይት ስታር” ተራድዖ ድርጅት ከጎናችን ሆኖ በአማራጭ መሠረታዊ ትምህርት በደረጃ 3 ለሦስት ዓመታት ያሰለጠናቸውን ከጎዳና ሕይወት የወጡ ልጆች አስመርቆ በማየቴ ደስ ብሎኛል ሲሉም ገልጸዋል ሚኒስትሯ፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.