Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ከቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት አስተሳሰብ እንድትወጣ ቻይና አሳሰበች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ከቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት አስተሳሰብ እንድትወጣ ቻይና አሳሰበች።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዩ እና የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በኢንዶኔዥያ እየተካሄደ ባለው የቡድን 20 ሀገራት ጉባኤ ጎን ለጎን ተወያይተዋል።

በውይይታቸው የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ “አሜሪካ የቻይናን የውጭ እና የውስጥ ፖሊሲ እንድታከብር፣ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ከመጣል እንድትቆጠብ እና የቀዝቃዛ ጦርነት አስተሳሰቧን እንድትተው” ትሻለች ብለዋል፡፡

አሜሪካ ቻይና በታይዋን ላይ ያላትን ሉዓላዊነት እንደማትደግፍ አንስተው ፥ “የአንድ ቻይና ፖሊሲን ለማፍረስ እና ለማጣመም እየሞከረች ነው” ሲሉም ዋንግ አሜሪካን ወቅሰዋል፡፡

ብሊንከን ከስብሰባ በኋላ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ ፥ “ሩሲያ በዩክሬን ላይ እያደረገች ነው ያሉትን ወታደራዊ ዘመቻ በማውገዝ ከአሜሪካና አጋሮቿ ጋር ቻይና አልተባበረችም እንዲሁም የምዕራቡ አለም በሞስኮ ላይ ማዕቀብ ሲጥል ከሩሲያ ጋር የንግድ ልውውጧን ይብስኑ አሳድጋለች፤ ገለልተኝነት ይጎላታል” ሲሉ ወቅሰዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.