Fana: At a Speed of Life!

ከአሌክሳንደር-ፑሺክን በጎፋ ማዞሪያ -ጎተራ የሚካሄደው የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአሌክሳንደር-ፑሺክን በጎፋ -ማዞሪያ ጎተራ አዲሱ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ግንባታ 99 በመቶ መድረሱ ተገለጸ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ እና ሌሎች አመራሮች በመንገድ ፕሮጀክቱ ላይ የአረንጓዴ ዐሻራ በማኖር የመንገዱን አአፈጻጸም ጎብኝተዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ መርሐ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በቅርቡ የሚመረቀው የመንገድ ፕሮጀክት በአካባቢውና በተለይም ቄራ ላይ ሲስተዋል የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቅረፍ ያስችላል ብለዋል፡፡
3 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር ርዝመትና ከ30 እስከ 40 ሜትር ስፋትያለው በዓይነቱ ለየት ያለ 320 ሜትር በላይ የሚረዝም እና በአራቱም አቅጣጫ መውጫ እንዲኖርው ተደርጎ ዘመናዊ የምድር ውስጥ የዋሻ መንገድ የተሰራለት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
የፈጣን አውቶብስን ጨምሮ የእግረኛና የብስክሌት መንገድ ደረጃውን ጠብቆ እየተገነባ መሆኑን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
የመንገድ ፕሮጀክቱ በቅርቡ ጥቃቅን ቀሪ ስራዎች ተጠናቀውለት ሙሉ በሙሉ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚደረግ የተናገሩት ከንቲባ አዳነች አቤቤ÷ ፕሮጀክቱ በተያዘለት ወቅት ምንም አይነት የገንዘብና የጊዜ ጭማሪ ሳይጠይቅ በነበረው ጥብቅ የስራ ክትትል በቅርቡ ሊጠናቀቅ መቃረቡን ገልጸዋል፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎችም አዲሱን የመንገድ ልማት ፕሮጀክት በመንከባከብና ለምግብነትም ሆነ ለጥላ የሚሆኑ ችግኞችን በመትከል ፕሮጀክቶቹን በቅንጅት እንዲያስውቡ ጥሪ አቅርበዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.