Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ አፍሪካ በምሽት መዝናኛ ቤት በተፈጸመ ጥቃት በጥቂቱ የ15 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ በምሽት መዝናኛ ቤት በተፈጸመ ጥቃት በጥቂቱ የ15 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ።
ጥቃቱ ትናንት ሌሊት የተፈጸመ ሲሆን በርካቶች መቁሰላቸውም ነው የተነገረው።
ጥቃት ፈጻሚዎቹ ከጥቃቱ በኋላ ከአካባቢው በተሽከርካሪ መሰወራቸው ታውቋል።
በሶዌቶ በተፈጸመው ጥቃት ለህልፈት የተዳረጉት ሰዎች ከ19 እስከ 35 አመት በሚገኝ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውንም ፖሊስ አስታውቋል።
በተመሳሳይ በሃገሪቱ ደቡብ ምስራቅ በምትገኘው ክዋዙሉ ናታል በተፈጸመ ሌላ ጥቃት አራት ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውንም ነው ፖሊስ የገለጸው።
ፖሊስ ከጥቃቶቹ ጋር በተያያዘ ምርመራ እያደረገ መሆኑን የአር ቲ እና ቢቢሲ ዘገባ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.