Fana: At a Speed of Life!

የጣና ሐይቅ ገዳማት፣ አድባራት፣ የተፈጥሮ እና የባሕል ቅርስን በዩኔስኮ በቋሚነት ለማስመዝገብ እየተሠራ ነው- የአማራ ክልል ቱሪዝም ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጣና ሐይቅ ገዳማት፣ አድባራት፣ የተፈጥሮ እና የባሕል ቅርስን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በቋሚነት ለማስመዝገብ እየተሠራ መሆኑን የአማራ ክልል ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡
የአማራ ክልል ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኤርሚያስ መኮንን÷ የጣና ሐይቅ ገዳማት፣ አድባራት፣ የተፈጥሮ እና የባሕል ቅርስ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት በጊዜያዊ መዝገብ መስፈራቸውን ጠቁመው እነዚህኑ ቅርሶች በቋሚነት ለማስመዝገብ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡
በጣና ሐይቅና አካባቢው ያሉ ሥፍራዎች የሃይማኖት እና የፍልስፍና ትምህርት ሲሰጥበት የኖረና የዓለም ምስጢራት ይገኙበታል ተብሎ የሚታሰብ መሆኑን ጠቅሰው÷ በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ሲደረግ የነበረው ጥረት ተቀባይነት አግኝቶ በጊዜያዊነት መመዝገቡን አስታውሰዋል፡፡
ቅርሶች በዓለም አቀፍ ተቋም ሲመዘገቡ ዓለም አቀፍ ጥበቃ እንደሚደረግላቸው እና በዓለም ዙሪያ እንደሚተዋወቁ እንዲሁም የምጣኔ ሃብት ምንጭ እንዲሆኑ ማድረግ ይቻላል ብለዋል፡፡
የጣና ሐይቅ ገዳማትና አድባራት በዓለም ቅርስነት ሲመዘገብ÷ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ባከበረና የኢትዮጵያን እሴት በጠበቀ መልኩ ነው ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
በቋሚነት ለማስመዝገብ በጥሩ ሂደት ላይ መሆኑን ጠቁመው÷ ቅርሱን በቋሚነት ለማስመዝገብ የሚደረገውን ጥረትም ተቋማት፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ሌሎች አካላት እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.