Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ካቢኔ የ2014 ዓ.ም የክልሉን የልማትና መልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈጻጸም እየገመገመ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) የ2014 በጀት ዓመት የክልሉን የልማትና መልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈጻጸም እየገመገመ ነው፡፡

በግምገማው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ የመስተዳድር ምክር ቤት የካቢኔ አባላት ተገኝተዋል፡፡

የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ እንዲሁም በአስተዳደር ክላስተሮች በዝርዝር ቀርቦ ጥልቅ ግምገማ እየተካሄደ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በግምገማው ላይ እንደገለጹት÷ የመድረኩ ዓላማ በበጀት ዓመቱ የተያዙ የልማት ግቦችና መሰረታዊ ተልዕኮዎችን በመገምገም ጥንካሬና ጉድለቶችን መለየት ነው።

ለ2015 በጀት ዓመት ከመልካም ልምዶች የምንማርበት እና ጥንካሬዎችንን የምናስቀጥልበት እንዲሁም ጉድለቶቻችንን ደግሞ በጽናት አርመን በቂ ዝግጅት በማድረግ ውጤታማ ሥራ ሠርተን የሕዝባችንን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መፍታት የምንችልበት ነው ብለዋል፡፡

ግምገማው÷ አመራሩ ለበለጠ ሥራ የሚነሳሳበት፣ የሚማማርበት፣ ለሕግ መከበርና ለዜጎች ሰላምና ደኅንነት መሰረት የሚጣልበት እና መሰረታዊ ችግሮችን በማረም ለላቀ ውጤት ዝግጅት የሚደረግበት የማጠቃለያ ምዕራፍ  መሆኑም ተመላክቷል፡፡

መድረኩ ለሁለት ተከታታይ ቀናት እንደሚካሄድ ተገልጿቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.