Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል ሙከራ ማድረጓን የደቡብ ኮሪያ ዜና አገልግሎት ዘገበ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል ሙከራ ማድረጓን የደቡብ ኮሪያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡
ዮንሃፕን ዋቢ ያደረገው የሺንዋ እና አር ቲ ዘገባ እንዳመላከተው የሚሳኤል ሙከራው ዛሬ ጠዋት የተደረገ ነው።
ሚሳኤሉ የተወነጨፈበት ስፍራም ሆነ የተወነጨፈው ሚሳኤል ቁጥር ግን እንዳልታወቀም ነው የዜና አገልግሎቱ የዘገበው።
ከደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ አዛዦች አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት እስካሁን ድረስ በሮኬት ማስወንጨፊያ የተተኮሱ ሁለት ሚሳኤሎች መለየታቸውንም ነው ዘገባው ያመላከተው።
ፒዮንግያንግ በፈረንጆቹ 2022 ከተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ በተቃራኒ ተደጋጋሚ የሚሳኤል ሙከራ ማድረጓን መረጃዎች ያመላክታሉ።
ደቡብ ኮሪያም በተጠናቀቀው ሰኔ ወር የመጀመሪያ ሳምንታት ጎረቤቷ ተደጋጋሚ ሚሳኤል አስወንጭፋለች በማለት ቅሬታዋን ስታቀርብ ቆይታለች።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.