Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአለታ ጩኮ ወረዳ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልላዊ መንግስት የእርሻ እና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ አስተባባሪነት የዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ማስጀመሪያ በአለታ ጩኮ ወረዳ ቴሶ ቀበሌ እየተካሄደ ነው።
 
በሲዳማ ክልል አለታ ጩኮ ወረዳ ቴሶ ቀበሌ ቦሪቴ መንደር ላይ አረንጓዴ አሻራ 4ኛው ዙር መርሐ ግብር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የሁሉም ወረዳዎችና ከተሞች የፊት አመራሮች በተገኙበት በመካሄድ ላይ መሆኑን ከሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ ህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.