Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ወደ አውሮፓ የምትልከውን የጋዝ ማስተላለፊያ መስመር ማቋረጧን አስታወቀች 

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በኖርድ ስትሪም – አንድ ወደ ጀርመን የተዘረጋውን የተፈጥሮ ጋዝ ማስተላለፊያ መስመር አገልግሎት ማቋረጧን አስታውቃለች፡፡

የጋዝ ማስተላለፊያ መስመሩ በመደበኛ ጥገና ምክንያት የጋዝ አቅርቦት ማቋረጡንም የስራ ሃላፊዎቹ ገልጸዋል።

መስመሩ ከዛሬ ጀምሮ ለ10 ቀናት አገልግሎት እንደማይሰጥም ነው የተገለጸው።

ከመስመሩ የአገልግሎት መቋረጥ ጋር በተያያዘ በሁለቱም ወገን በኩል ስምምነት መደረሱንም አስታውቀዋል።

ባለፈው ወር ግዙፉ የሩሲያ የጋዝ ኩባንያ ጋዝፕሮም በኖርድ ማስተላለፊያ መስመር- አንድ የተፈጥሮ ጋዝ ቧንቧ ማስተላለፊያ መስመር መዝጋቱ ይታወሳል።

በዚህም ለጀርመን የሚያቀርበውን የጋዝ አቅርቦት መጠን በ60 በመቶ እንዲቀንስ ማድረጉን አር ቲ በዘገባው አስታውሷል።

ኩባንያው ለመስመሩ መዘጋት ጊዜያዊና መደበኛ ጥገና ምክንያት መሆናቸውን ቢገልጽም፥ የጀርመን ኢኮኖሚ ሚኒስትር ሮበርት ሃቤክ የኩባንያውን ድርጊት “ፖለቲካዊ ውሳኔ ነው” ነው ብለውታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.