Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ዘላቂ የትራንስፖርት አማራጭ ስርዓቶችን ጥቅም ላይ ማዋልን እንደምታበረታታ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ሐምሌ 4፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ አረንጓዴ እና ዘላቂ የትራንስፖርት አማራጭ ስርዓቶችን ጥቅም ላይ ማዋልን እንደምታበረታታ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ገለጹ፡፡

ሚኒስትሯ በኢትዮጵያ ስላለው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ምቹ ገበያ በሚመለከት ከዶዳይ ግሩፕ የሥራ ሃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ ኢትዮጵያ አረንጓዴ እና ዘላቂ የትራንስፖርት አማራጭ ስርዓቶችን ጥቅም ላይ ማዋልን እንደምታበረታታ እና በስትራቴጂና ፖሊሲዋ ላይም በግልፅ ማስቀመጧን ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ጠቅሰዋል፡፡

በ10 አመት የልማት እቅድ በሺህዎች የሚቆጠሩ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውቶብሶችን እና አነስተኛ ተሽከርካሪዎችን ለማስፋፋት እቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በስፋት ወደ ገበያው ለማስገባት ከግሉ የአውቶሞቲቭ ዘርፍ ጋር በቅርበት እየሰራን ነው ማለታቸውን ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የተለያዩ ማበረታቻዎችን በመዘርጋት ጭምር የግል ባለሀብቶች በዘርፉ እንዲሰማሩ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለውም ገልፀዋል፡፡

የዶዳይ ግሩፕ የሥራ ሃላፊዎች በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በስፋት እንደሚያስፈልጋት በማመን ዘርፉን መቀላቀላቸውን ተናግረዋል፡፡

የትራንስፖትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አምራች ባለሀብቶች ወደ ገበያ በስፋት እንዲገቡ እያደረገ ያለው ጥረት የሚመሰገን መሆኑን ጠቅሰው÷ በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.