Fana: At a Speed of Life!

የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ በማዘጋጀት ረገድ ኢትዮጵያ ስኬታማ ተሞክሮ አላት -ዶ/ር እዮብ ተካልኝ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ በማዘጋጀት ረገድ ኢትዮጵያ ስኬታማ ተሞክሮ ያላት መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ ተናገሩ፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው የእዳ ተጋላጭነትን በመቅረፍ ዘላቂ የፋይናንስ አሰራርን ለመተግበር በተዘጋጀው 9ኛው የፓሪስ ፎረም ላይ ተሳተፈዋል፡፡

በፎረሙ ኢትዮጵያ የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ በማዘጋጀት ረገድ ስኬታማ ተሞክሮ ያላት መሆኑን ዶክተር እዮብ አስረድተዋል፡፡

ይህም ዘላቂ የሆነ የፋይናንስ አሰራርን ተግበራዊ ለማድረግ እና የብድር ዕዳን ለማስተዳደር የላቀ ሚና እንዳለው ነው ያመላከቱት፡፡

ዶክተር እዮብ አበዳሪ ተቋማት የቡድን 20 አባል አገራት ግልፅ የሆነ የጊዜ ገደብ በማዘጋጀት የእዳ አያያዝ ማዕቀፍን ለማጠናቀቅ የሚደርጉትን ጥረት እንዲያግዙ መጠየቃቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በፎረሙ የእዳ ተጋላጭነትን ለመቀነስ እና የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ለመፍጠር መንግስት በያዘው የአጭር ጊዜ እቅድ መሰረት በእዳ አያያዝ ማዕቀፍ የብድር ማመጣጠን እንዲደረግላት ተጠይቋል፡፡

 

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.