Fana: At a Speed of Life!

በክረምት ስራዎቻችን የዘመሙ ጎጆዎችን እያቀናን፣ የደከሙትን እያጠናከርንና የታረዙትን እያለበስን አንድነታችንን እናጠናክራለን” – ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  “በክረምት ስራዎቻችን የዘመሙ ጎጆዎችን እያቀናን፣ የደከሙትን እያጠናከርንና የታረዙትን እያለበስን አንድነታችንን እናጠናክራለን ”ሲሉ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ተናገሩ፡፡

ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፥   “ሲተርፈን ሳይሆን ካለን ላይ ማካፈል የኢትዮጵያዊነት እሴት ነው” ብለዋል።

አክለውም እንደ ሴክተር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን እና የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ስራን ቀደም ሲል በአንጋፋው የተግባረ ዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ፣  ዛሬ ደግሞ በሆለታ ፖሊ ቴክኒክ ተገኝተው መሐ ግብሩን ማስጀመራቸውን ገልፀዋል፡፡

ሚኒስቴሩ በተያዘው ክረምት በአዲስ አበባ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ 42 እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ 300 ቤቶችን ለማደስ እቅድ መያዙንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

በአጠቃላይ 1 ሺህ 428 የአቅመ ደካሞች ቤቶችን ለማደስ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል እቅድ መያዙንም ነው ሚኒስትሯ ያመላከቱት፡፡

“‘ከተረፈን ሳይሆን ካለን ላይ በማካፈል ማዕድ እናጋራለን’” ያሉት ሚኒስትሯ፥  “በክረምት ስራዎቻችን የዘመሙ ጎጆዎችን እያቀናን፣ የደከሙትን እያጠናከርንና የታረዙትን እያለበስን አንድነታችንን እናጠናክራለን” ሲሉም ነው የገለጹት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.