Fana: At a Speed of Life!

አየርላንድ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል አንድ ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አየርላንድ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል ተጨማሪ አንድ ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገች፡፡

አየርላንድ ያደረገችው ድጋፍ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ችግር ውስጥ ለሚገኙ እና አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚውል መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር በኩል የሚሰራጨው ይህ ድጋፍ÷ በኢትዮጵያ የሚደረገውን የሰብአዊ እርዳታ ምላሸ ለማሳደግ እንደሚያስችል ከአየርላንድ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.