Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ በተከሰተው ጭጋጋማ የአየር ፀባይ ምክንያት ተቋርጠው ከነበሩት በረራዎች አብዛኛዎቹ ተጀምረዋል – የኢትዮጵያ አየር መንገድ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ በተከሰተው ጭጋጋማ የአየር ጸባይ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የአውሮፕላን በረራ በአብዛኛው መጀመሩን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ፡፡

አየር መንገዱ ባለፉት ጥቂት ሰአታት በአዲስ አበባ የነበረው ጭጋጋማ የአየር ፀባይ መሻሻል ማሳየቱን ጠቁሟል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም መዳረሻቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ በረራዎች አብዛኛዎቹ መደረጋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

በተጨማሪም ከአዲስ አበባ ተነስተው ወደ ተለያዩ ሃገራት የሚደረጉ በረራዎች ተጀምረዋልም ነው ያለው።

አያይዞም ለደንበኞቹ ተጨማሪ መረጃዎች ማድረሱን እንደሚቀጥልም ገልጿል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.