Fana: At a Speed of Life!

ዴሞክራሲ ለኢትዮጵያ ምርጫ ሳይሆን ሀገር የመገንባት ጉዳይ ነው- አቶ ተስፋዬ በልጅጌ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዴሞክራሲ ለኢትዮጵያ ምርጫ ሳይሆን ሀገር የመገንባት ጉዳይ ነው ሲሉ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ገለጹ፡፡

ምክር ቤቱ ከዴሞክራሲ ተቋማት ጋር እያካሄደ በሚገኘው የጋራ ፎረም ላይ የመንግስት ዋና ተጠሪው አቶ ተስፋዬ በልጅጌ  በሰጡት አስተያየት÷ የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ የዴሞክራሲ ባሕል ግንባታ ስራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ገለልተኛ የዴሞክራሲ ተቋማትን ለመገንባት የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቅሰው፥ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ጠንካራ ተቋማትን ለመገንባት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ትኩረት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

እንደ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ገለጻ÷ ለአብነትም በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና በዕንባ ጠባቂ ተቋም በኩል ለውጥ ለማምጣት ታልመው የተከናወኑት ሥራዎች አበረታች ናቸው፡፡

የሰብዓዊ መብት እና የዕንባ ጠባቂ ተቋም የሪፎርም ሥራዎች አተገባበር እና ተቋማቱን ለማጠናከር የተሠሩ ስራዎች እንዲሁም ጥንካሬ እና ድክመቶች ተለይተው ለጋራ ፎረሙ መቅረባቸውንም ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.